ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መክብብ 1:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በኢየሩሳሌም የነገሠው፣ የዳዊት ልጅ፣ የሰባኪው ቃል፤

2. ሰባኪው፣“ከንቱ፣ ከንቱ፣የከንቱ ከንቱ፤ሁሉም ነገር ከንቱ ነው” ይላል።

3. ከፀሓይ በታች ከሚለፋበት ተግባር ሁሉ፣ሰው ምን ትርፍ ያገኛል?

4. ትውልድ ይሄዳል፤ ትውልድ ይመጣል፤ምድር ግን ለዘላለም ጸንታ ትኖራለች።

5. ፀሓይ ትወጣለች፤ ትጠልቃለችም፤ወደምትወጣበትም ለመመለስ ትጣደፋለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መክብብ 1