የጥንት ዘመን ሰዎች ወደ ገቡበት ጒድጓድ ከሚወርዱት ጋር አወርድሻለሁ፤ ወደ ጒድጓድ ከሚወርዱት ጋር በጥንቱ ፍርስራሽ ከምድር በታች አኖርሻለሁ፤ ከዚህም በኋላ በሕያዋን ምድር ተመልሰሽ ቦታ አታገኚም፤