ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 26:18-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. አሁን በመውደቂያሽ ቀን፣በጠረፍ ያሉ አገሮች ተናወጡ፤ከመፍረስሽም የተነሣ፤በባሕር ውስጥ ያሉ ደሴቶች ተደናገጡ።”

19. “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሰው እንደማይኖርባቸው ከተሞች ባድማ ሳደርግሽ፣ የውቅያኖስንም ውሃ በላይሽ አድርጌ በቀላይ ስሸፍንሽ፣

20. የጥንት ዘመን ሰዎች ወደ ገቡበት ጒድጓድ ከሚወርዱት ጋር አወርድሻለሁ፤ ወደ ጒድጓድ ከሚወርዱት ጋር በጥንቱ ፍርስራሽ ከምድር በታች አኖርሻለሁ፤ ከዚህም በኋላ በሕያዋን ምድር ተመልሰሽ ቦታ አታገኚም፤

21. መጨረሻሽን አሳዛኝ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህም አትኖሪም፤ ትፈለጊያለሽ፤ ከቶም አትገኚም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 26