ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 26:16-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. የባሕር ጠረፍ መሳፍንት ሁሉ ከዙፋኖቻቸው ይወርዳሉ፤ መጐናጸፊያቸውን ይጥላሉ፤ ወርቀ ዘቦ ልብሳቸውን ያወልቃሉ። ፍርሀት ተከናንበው በመሬት ላይ በመቀመጥ ባለማቋረጥ፣ እየተንቀጠቀጡ በአንቺ ላይ በደረሰው ነገር ይሸበራሉ፤’

17. ስለ አንቺም እንዲህ ብለው ሙሾ ያወርዳሉ፤“በባሕር ሰዎች የሚኖሩብሽ፣ባለዝናዋ ከተማ ሆይ፤ እንዴት ጠፋሽ!ከነዋሪዎችሽ ጋር፣የባሕር ላይ ኀያል ነበርሽ፤በዚያ በሚኖሩትም ሁሉ ዘንድየተፈራሽ ነበርሽ።

18. አሁን በመውደቂያሽ ቀን፣በጠረፍ ያሉ አገሮች ተናወጡ፤ከመፍረስሽም የተነሣ፤በባሕር ውስጥ ያሉ ደሴቶች ተደናገጡ።”

19. “ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ሰው እንደማይኖርባቸው ከተሞች ባድማ ሳደርግሽ፣ የውቅያኖስንም ውሃ በላይሽ አድርጌ በቀላይ ስሸፍንሽ፣

20. የጥንት ዘመን ሰዎች ወደ ገቡበት ጒድጓድ ከሚወርዱት ጋር አወርድሻለሁ፤ ወደ ጒድጓድ ከሚወርዱት ጋር በጥንቱ ፍርስራሽ ከምድር በታች አኖርሻለሁ፤ ከዚህም በኋላ በሕያዋን ምድር ተመልሰሽ ቦታ አታገኚም፤

21. መጨረሻሽን አሳዛኝ አደርጋለሁ፤ ከእንግዲህም አትኖሪም፤ ትፈለጊያለሽ፤ ከቶም አትገኚም፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።’ ”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 26