ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሕዝቅኤል 23:34-37 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

34. ትጠጪዋለሽ፤ ትጨልጪዋለሽም፤ከዚያም ጽዋውን ትሰባብሪዋለሽ፤ጡትሽንም ትቈራርጪአለሽ፤እኔ ተናግሬአለሁ፤ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።

35. “ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ረስተሽኛል፤ ወደ ኋላም ገሸሽ አድርገሽኛልና የብልግናሽንና የሴሰኝነትሽን ውጤት ትሸከሚአለሽ።’

36. እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “የሰው ልጅ ሆይ፤ በኦሖላና በኦሖሊባ ትፈርዳለህን? እንግዲያውስ ጸያፍ ተግባራቸውን ንገራቸው።

37. አመንዝረዋል እጃቸውም በደም ተበክሎአልና። ከጣዖቶቻቸው ጋር አመነዘሩ፤ የወለዱልኝን ልጆቻቸውን እንኳ ለእነርሱ መብል ይሆኑ ዘንድ በእሳት ሠውተውላቸዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሕዝቅኤል 23