ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 8:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. “ነፋስን ይዘራሉ፤ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤አገዳው ዛላ የለውም፤ዱቄትም አይገኝበትም፤እህል አፍርቶ ቢገኝም፣ባዕዳን ይበሉታል።

8. እስራኤል ተውጠዋል፤በአሕዛብም መካከል፣ዋጋ እንደሌለው ዕቃ ሆነዋል።

9. ለብቻው እንደሚባዝን የዱር አህያ፣ወደ አሦር ሄደዋልና፤ኤፍሬም በእጅ መንሻ ወዳጅ አበጀ።

10. በአሕዛብ መካከል ራሳቸውን ቢሸጡም፣እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤በኀያል ንጉሥ ጭቈና ሥር፣እየመነመኑ ይሄዳሉ።

11. “ኤፍሬም ለኀጢአት ማስተስረያ ብዙ መሠዊያዎችን ቢሠራም፣እነርሱ የኀጢአት መሥሪያ መሠዊያዎች ሆነውበታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 8