ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

እስራኤል ዐውሎ ነፋስን ታጭዳለች

1. “መለከትን በአፍህ ላይ አድርግ፤ሕዝቡ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና፣በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና፣ንስር በእግዚአብሔር ቤት ላይ ነው፤

2. እስራኤልም፣ ‘አምላካችን ሆይ፤ እኛ እናውቅሃለን’ እያሉ፣ወደ እኔ ይጮኻሉ።

3. ነገር ግን እስራኤል በጎ የሆነውን ነገር ናቁ፤ጠላትም ያሳድዳቸዋል።

4. ያለ እኔ ፈቃድ ነገሥታትን አነገሡ፤እኔንም ሳይጠይቁ አለቆችን መረጡ፤በብራቸውና በወርቃቸው፣ለገዛ ጥፋታቸው፣ጣዖታትን ለራሳቸው ሠሩ።

5. ሰማርያ ሆይ፤ የጥጃ ጣዖትሽን ጣይ፤ቊጣዬ በእነርሱ ላይ ነድዶአል፤የማይነጹት እስከ መቼ ነው?

6. ይህም በእስራኤል ሆነ!ባለ እጅ የሠራው ይህ ጥጃ፣ አምላክአይደለም፤ያ የሰማርያ ጥጃ፣ተሰባብሮ ይደቃል።

7. “ነፋስን ይዘራሉ፤ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤አገዳው ዛላ የለውም፤ዱቄትም አይገኝበትም፤እህል አፍርቶ ቢገኝም፣ባዕዳን ይበሉታል።

8. እስራኤል ተውጠዋል፤በአሕዛብም መካከል፣ዋጋ እንደሌለው ዕቃ ሆነዋል።

9. ለብቻው እንደሚባዝን የዱር አህያ፣ወደ አሦር ሄደዋልና፤ኤፍሬም በእጅ መንሻ ወዳጅ አበጀ።

10. በአሕዛብ መካከል ራሳቸውን ቢሸጡም፣እኔ አሁን እሰበስባቸዋለሁ፤በኀያል ንጉሥ ጭቈና ሥር፣እየመነመኑ ይሄዳሉ።

11. “ኤፍሬም ለኀጢአት ማስተስረያ ብዙ መሠዊያዎችን ቢሠራም፣እነርሱ የኀጢአት መሥሪያ መሠዊያዎች ሆነውበታል።

12. በሕጌ ውስጥ ያለውን ብዙውን ነገር ጻፍሁላቸው፤እነርሱ ግን እንደ እንግዳ ነገር ቈጠሩት።

13. ለእኔ የሚገባውን መሥዋዕት ያቀርባሉ፤ሥጋውንም ይበላሉ፤ እግዚአብሔር ግን በእነርሱ አልተደሰተም፤ስለዚህ ክፋታቸውን ያስታውሳል፤ኀጢአታቸውን ይቀጣል፤ወደ ግብፅም ይመለሳሉ።

14. እስራኤል ፈጣሪውን ረሳ፤ቤተ መንግሥቶችንም ሠራ፤ይሁዳም የተመሸጉ ከተሞችን አበዛ፤እኔ ግን በከተሞቻቸው ላይ እሳትን እለቃለሁ፤ምሽጎቻቸውንም ይበላል።”