ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 8:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ሰማርያ ሆይ፤ የጥጃ ጣዖትሽን ጣይ፤ቊጣዬ በእነርሱ ላይ ነድዶአል፤የማይነጹት እስከ መቼ ነው?

6. ይህም በእስራኤል ሆነ!ባለ እጅ የሠራው ይህ ጥጃ፣ አምላክአይደለም፤ያ የሰማርያ ጥጃ፣ተሰባብሮ ይደቃል።

7. “ነፋስን ይዘራሉ፤ዐውሎ ነፋስንም ያጭዳሉ፤አገዳው ዛላ የለውም፤ዱቄትም አይገኝበትም፤እህል አፍርቶ ቢገኝም፣ባዕዳን ይበሉታል።

8. እስራኤል ተውጠዋል፤በአሕዛብም መካከል፣ዋጋ እንደሌለው ዕቃ ሆነዋል።

9. ለብቻው እንደሚባዝን የዱር አህያ፣ወደ አሦር ሄደዋልና፤ኤፍሬም በእጅ መንሻ ወዳጅ አበጀ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 8