ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 8:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. “መለከትን በአፍህ ላይ አድርግ፤ሕዝቡ ቃል ኪዳኔን አፍርሰዋልና፣በሕጌም ላይ ዐምፀዋልና፣ንስር በእግዚአብሔር ቤት ላይ ነው፤

2. እስራኤልም፣ ‘አምላካችን ሆይ፤ እኛ እናውቅሃለን’ እያሉ፣ወደ እኔ ይጮኻሉ።

3. ነገር ግን እስራኤል በጎ የሆነውን ነገር ናቁ፤ጠላትም ያሳድዳቸዋል።

4. ያለ እኔ ፈቃድ ነገሥታትን አነገሡ፤እኔንም ሳይጠይቁ አለቆችን መረጡ፤በብራቸውና በወርቃቸው፣ለገዛ ጥፋታቸው፣ጣዖታትን ለራሳቸው ሠሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 8