ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 7:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እስራኤልን በምፈውስበት ጊዜ፣የኤፍሬም ኀጢአት፣የሰማርያም ክፋት ይገለጣል።እነርሱ ያጭበረብራሉ፤ሌቦች ቤቶችን ሰብረው ይገባሉ፤ወንበዴዎችም በየመንገድ ይዘርፋሉ።

2. ነገር ግን ክፉ ድርጊታቸውን ሁሉ እንደማስታውስ፣እነርሱ አይገነዘቡም፤ኀጢአታቸው ከቦአቸዋል፤ሁልጊዜም በፊቴ ናቸው።

3. “ንጉሡን በክፋታቸው፣አለቆችንም በሐሰታቸው ያስደስታሉ።

4. ሊጡ ቦክቶ ኩፍ እንደሚል፣ዳቦ ጋጋሪው እሳት መቈስቈስ እስከማያስፈልገው ድረስ፣እንደሚነድ ምድጃ፣ሁሉም አመንዝራ ናቸው።

5. በንጉሣችን የበዓል ቀን፣አለቆች በወይን ጠጅ ስካር ጋሉ፤እርሱም ከፌዘኞች ጋር ተባበረ።

6. ልባቸው እንደ ምድጃ የጋለ ነው፤በተንኰል ይቀርቡታል፤ቍጣቸው ሌሊቱን ሙሉ ይጤሳል፤እንደሚነድም እሳት በማለዳ ይንበለበላል።

7. ሁሉም እንደ ምድጃ የጋሉ ናቸው፤ገዦቻቸውን ፈጁ፤ንጉሦቻቸው ሁሉ ወደቁ፤ከእነርሱም ወደ እኔ የቀረበ ማንም የለም።

8. “ኤፍሬም ከአሕዛብ ጋር ተደባለቀ፤ኤፍሬም ያልተገላበጠ ቂጣ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 7