ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 5:9-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. በቅጣት ቀን፣ኤፍሬም ባድማ ይሆናል፣በእስራኤል ነገዶች መካከል፣በእርግጥ የሚሆነውን ዐውጃለሁ።

10. የይሁዳ መሪዎች፣የወሰን ድንጋዮችን እንደሚነቅሉ ሰዎች ናቸው፤እንደ ጐርፍ ውሃ፣ቊጣዬን በላያቸው ላይ አፈስሳለሁ።

11. ጣዖትን መከተል በመውደዱ፣ኤፍሬም ተጨቊኖአል፤በፍርድም ተረግጦአል።

12. እኔ ለኤፍሬም እንደ ብል፣ለይሁዳም ሕዝብ እንደ ነቀዝ ሆኛለሁ።

13. “ኤፍሬም ሕመሙን፣ይሁዳም ቊስሉን ባየ ጊዜ፣ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ርዳታ ለመጠየቅ ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤እርሱ ግን ሊያድናችሁ፣ቊስላችሁንም ሊፈውስ አይችልም።

14. እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ለይሁዳም እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና፤ሰባብሬና አድቅቄአቸው እሄዳለሁ፤ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።

15. በደላቸውንም እስኪያውቁ ድረስ፣ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፤ፊቴን ይሻሉ፤በመከራቸውም አጥብቀውይፈልጉኛል።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 5