ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

በእስራኤል ላይ የተነገረ ፍርድ

1. “እናንተ ካህናት፤ ይህን ስሙ!እናንት እስራኤላውያን፤ አስተውሉ!የንጉሥ ቤት ሆይ፤ ስሙ!ይህ ፍርድ በእናንተ ላይ ነው፤በምጽጳ ወጥመድ፣በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋልና።

2. ዐመፀኞች በግድያ በርትተዋል፤ሁሉንም እቀጣቸዋለሁ።

3. ስለ ኤፍሬም ሁሉን ዐውቃለሁ፤እስራኤልም ከእኔ የተሰወረች አይደለችም፤ኤፍሬም፣ አንተ አሁን አመንዝረሃል፤እስራኤልም ረክሳለች።

4. “የሠሩት ሥራ፣ ወደ አምላካቸው እንዲመለሱአይፈቅድላቸውም፤የአመንዝራነት መንፈስ በልባቸው አለ፤ እግዚአብሔርንም አያውቁትም።

5. የእስራኤል ትዕቢት በራሷ ላይ ይመሰክራል፤እስራኤላውያንና ኤፍሬምም በኀጢአታቸው ይሰናከላሉ፤ይሁዳም ደግሞ አብሮአቸው ይሰናከላል።

6. እግዚአብሔርን ለመሻት፣የበግና የፍየል መንጋ እንዲሁም የቀንድ ከብቶቻቸውን ነድተው ሲሄዱ፣እርሱ ስለ ተለያቸው፣ሊያገኙት አይችሉም።

7. ለእግዚአብሔር ታማኞች አልሆኑም፤ዲቃሎች ወልደዋልና፤ስለዚህ የወር መባቻ በዓላቸው፤እነርሱንና ዕርሻቸውን ያጠፋል።

8. “በጊብዓ መለከትን፣በራማ እንቢልታን ንፉ፤በቤትአዌን የማስጠንቀቂያ ድምፅ አሰሙ፤‘ብንያም ሆይ፤ መጡብህ!’ በሉ።

9. በቅጣት ቀን፣ኤፍሬም ባድማ ይሆናል፣በእስራኤል ነገዶች መካከል፣በእርግጥ የሚሆነውን ዐውጃለሁ።

10. የይሁዳ መሪዎች፣የወሰን ድንጋዮችን እንደሚነቅሉ ሰዎች ናቸው፤እንደ ጐርፍ ውሃ፣ቊጣዬን በላያቸው ላይ አፈስሳለሁ።

11. ጣዖትን መከተል በመውደዱ፣ኤፍሬም ተጨቊኖአል፤በፍርድም ተረግጦአል።

12. እኔ ለኤፍሬም እንደ ብል፣ለይሁዳም ሕዝብ እንደ ነቀዝ ሆኛለሁ።

13. “ኤፍሬም ሕመሙን፣ይሁዳም ቊስሉን ባየ ጊዜ፣ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ርዳታ ለመጠየቅ ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤እርሱ ግን ሊያድናችሁ፣ቊስላችሁንም ሊፈውስ አይችልም።

14. እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ለይሁዳም እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና፤ሰባብሬና አድቅቄአቸው እሄዳለሁ፤ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።

15. በደላቸውንም እስኪያውቁ ድረስ፣ወደ ስፍራዬ እመለሳለሁ፤ፊቴን ይሻሉ፤በመከራቸውም አጥብቀውይፈልጉኛል።”