ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 5:8-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. “በጊብዓ መለከትን፣በራማ እንቢልታን ንፉ፤በቤትአዌን የማስጠንቀቂያ ድምፅ አሰሙ፤‘ብንያም ሆይ፤ መጡብህ!’ በሉ።

9. በቅጣት ቀን፣ኤፍሬም ባድማ ይሆናል፣በእስራኤል ነገዶች መካከል፣በእርግጥ የሚሆነውን ዐውጃለሁ።

10. የይሁዳ መሪዎች፣የወሰን ድንጋዮችን እንደሚነቅሉ ሰዎች ናቸው፤እንደ ጐርፍ ውሃ፣ቊጣዬን በላያቸው ላይ አፈስሳለሁ።

11. ጣዖትን መከተል በመውደዱ፣ኤፍሬም ተጨቊኖአል፤በፍርድም ተረግጦአል።

12. እኔ ለኤፍሬም እንደ ብል፣ለይሁዳም ሕዝብ እንደ ነቀዝ ሆኛለሁ።

13. “ኤፍሬም ሕመሙን፣ይሁዳም ቊስሉን ባየ ጊዜ፣ኤፍሬም ወደ አሦር ሄደ፤ርዳታ ለመጠየቅ ወደ ታላቁ ንጉሥ መልእክተኛ ላከ፤እርሱ ግን ሊያድናችሁ፣ቊስላችሁንም ሊፈውስ አይችልም።

14. እኔ ለኤፍሬም እንደ አንበሳ፣ለይሁዳም እንደ ደቦል አንበሳ እሆናለሁና፤ሰባብሬና አድቅቄአቸው እሄዳለሁ፤ነጥቄ እወስዳቸዋለሁ፤ ማንም ሊያድናቸው አይችልም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 5