ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 2:13-23 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ለበኣል አማልክት፣ ዕጣን ስላጠነችባቸው ቀናትእቀጣታለሁ፤በጌጣ ጌጥና በቀለበቶች ራሷን አስጊጣለች፤ውሽሞቿንም ተከትላ ሄዳለች፤እኔን ግን ረስታለች”ይላል እግዚአብሔር።

14. “ስለዚህ እነሆ፤ አባብላታለሁ፤ወደ ምድረ በዳም እወስዳታለሁ፤በፍቅር ቃል አነጋግራታለሁ።

15. በዚያም የወይን ተክሏን እመልስላታለሁ፤የአኮርንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ።በዚያም ከግብፅ እንደ ወጣችበት ቀን፣እንደ ልጅነቷም ጊዜ ትዘምራለች።

16. “በዚያ ቀን፣ ‘ባሌ’ ብለሽ፣ትጠሪኛለሽ” ይላል እግዚአብሔር።“ከእንግዲህም፣ ‘ጌታዬ’ ብለሽ አትጠሪኝም።

17. የበኣል አማልክትን ስም ከአንደበቷ አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም ስሞቻቸው አይነሡም።

18. በዚያን ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች፣በምድርም ላይ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረት ጋር፣ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ፤ሁሉም በሰላም እንዲኖሩ፣ቀስትን፣ ሰይፍንና ጦርነትን፣ከምድሪቱ አስወግዳለሁ።

19. ለእኔ እንድትሆኚ ለዘላለም አጭሻለሁ፤በጽድቅና በፍትሕ፣በፍቅርና በርኅራኄም አጭሻለሁ።

20. በታማኝነት አጭሻለሁ፤አንቺም እግዚአብሔርን ታውቂያለሽ።

21. እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“በዚያ ቀን እኔ እመልሳለሁ፤ለሰማያት እመልሳለሁ፤እነርሱም ለምድር ምላሽ ይሰጣሉ፤

22. ምድርም ለእህል፣ለአዲስ የወይን ጠጅና ለዘይት ምላሽ ትሰጣለች፤እነርሱም ለኢይዝራኤል ምላሽ ይሰጣሉ።

23. ስለ ራሴ ስል በምድሪቱ እተክላታለሁ፤‘ምሕረትን ያላገኘ’ ብዬ የጠራሁትንም እምረዋለሁ፤‘ሕዝቤ አይደላችሁም’ ተብለው የተጠሩትንም፣ ‘ሕዝቤ’ እላቸዋለሁ፤እነርሱም፣ ‘አንተ አምላኬ ነህ’ ይላሉ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 2