ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 2:11-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. የደስታ በዓሎቿን ሁሉ፣የዓመት በዓሎቿንና፣ የወር መባቻዎቿንሰንበቶቿንና የተመረጡ በዓሎቿን ሁሉ አስቀራለሁ።

12. ከውሽሞቼ የተቀበልሁት ዋጋ ነው የምትለውን፤የወይን ተክሎቿንና የበለስ ዛፎቿን አጠፋለሁ፤ጫካ አደርገዋለሁ፤የዱር አራዊትም ይበሉታል።

13. ለበኣል አማልክት፣ ዕጣን ስላጠነችባቸው ቀናትእቀጣታለሁ፤በጌጣ ጌጥና በቀለበቶች ራሷን አስጊጣለች፤ውሽሞቿንም ተከትላ ሄዳለች፤እኔን ግን ረስታለች”ይላል እግዚአብሔር።

14. “ስለዚህ እነሆ፤ አባብላታለሁ፤ወደ ምድረ በዳም እወስዳታለሁ፤በፍቅር ቃል አነጋግራታለሁ።

15. በዚያም የወይን ተክሏን እመልስላታለሁ፤የአኮርንም ሸለቆ የተስፋ በር እንዲሆናት አደርጋለሁ።በዚያም ከግብፅ እንደ ወጣችበት ቀን፣እንደ ልጅነቷም ጊዜ ትዘምራለች።

16. “በዚያ ቀን፣ ‘ባሌ’ ብለሽ፣ትጠሪኛለሽ” ይላል እግዚአብሔር።“ከእንግዲህም፣ ‘ጌታዬ’ ብለሽ አትጠሪኝም።

17. የበኣል አማልክትን ስም ከአንደበቷ አስወግዳለሁ፤ከእንግዲህም ስሞቻቸው አይነሡም።

18. በዚያን ቀን ከምድር አራዊትና ከሰማይ ወፎች፣በምድርም ላይ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረት ጋር፣ቃል ኪዳን አደርግላቸዋለሁ፤ሁሉም በሰላም እንዲኖሩ፣ቀስትን፣ ሰይፍንና ጦርነትን፣ከምድሪቱ አስወግዳለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 2