ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 13:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኤፍሬም ሲናገር ሰዎች ተንቀጠቀጡ፤በእስራኤልም የተከበረ ነበር፤ነገር ግን በኣልን ስላመለከ በደለ፤ ሞተም።

2. አሁንም ኀጢአትን መሥራት አበዙ፤ብራቸውን አቅልጠው ለራሳቸው ጣዖት ሠሩ፣በጥበብ የተሠሩ ምስሎችን አበጁ፤ሁሉም የባለ እጅ ሥራ ናቸው።ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ተብሎአል፤“ሰውን መሥዋዕት አድርገው ያቀርባሉ፤የጥጃ ጣዖቶችንም ይስማሉ”

3. ስለዚህ እንደ ማለዳ ጉም፣ፈጥኖ እንደሚጠፋ የጧት ጤዛ፣ከዐውድማ እንደሚጠረግ ዕብቅ፣በመስኮትም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ።

4. “እኔ ግን ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ፤ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም፤ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ የለም።

5. በምድረ በዳ፣በሐሩር ምድርም ተንከባከብሁህ።

6. ካበላኋቸው በኋላ ጠገቡ፤በጠገቡ ጊዜ ታበዩ፤ከዚያም ረሱኝ።

7. ስለዚህ እንደ አንበሳ እመጣባቸዋለሁ፤እንደ ነብርም በመንገድ አደባባቸዋለሁ።

8. ግልገሎቿን እንደ ተነጠቀች ድብ፣እመታቸዋለሁ፤ እዘነታትላቸዋለሁ።እንደ አንበሳም ሰልቅጬ እውጣቸዋለሁ፤የዱር አራዊትም ይገነጣጥላቸዋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 13