ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የእግዚአብሔር ቊጣ በእስራኤል ላይ

1. ኤፍሬም ሲናገር ሰዎች ተንቀጠቀጡ፤በእስራኤልም የተከበረ ነበር፤ነገር ግን በኣልን ስላመለከ በደለ፤ ሞተም።

2. አሁንም ኀጢአትን መሥራት አበዙ፤ብራቸውን አቅልጠው ለራሳቸው ጣዖት ሠሩ፣በጥበብ የተሠሩ ምስሎችን አበጁ፤ሁሉም የባለ እጅ ሥራ ናቸው።ስለ እነዚህ ሰዎች እንዲህ ተብሎአል፤“ሰውን መሥዋዕት አድርገው ያቀርባሉ፤የጥጃ ጣዖቶችንም ይስማሉ”

3. ስለዚህ እንደ ማለዳ ጉም፣ፈጥኖ እንደሚጠፋ የጧት ጤዛ፣ከዐውድማ እንደሚጠረግ ዕብቅ፣በመስኮትም እንደሚወጣ ጢስ ይሆናሉ።

4. “እኔ ግን ከግብፅ ምድር ያወጣሁህ፣አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ፤ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም፤ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ የለም።

5. በምድረ በዳ፣በሐሩር ምድርም ተንከባከብሁህ።

6. ካበላኋቸው በኋላ ጠገቡ፤በጠገቡ ጊዜ ታበዩ፤ከዚያም ረሱኝ።

7. ስለዚህ እንደ አንበሳ እመጣባቸዋለሁ፤እንደ ነብርም በመንገድ አደባባቸዋለሁ።

8. ግልገሎቿን እንደ ተነጠቀች ድብ፣እመታቸዋለሁ፤ እዘነታትላቸዋለሁ።እንደ አንበሳም ሰልቅጬ እውጣቸዋለሁ፤የዱር አራዊትም ይገነጣጥላቸዋል።

9. “እስራኤል ሆይ፤ በእኔ ላይ ስለ ተነሣህ፣ረዳትህንም ስለ ተቃወምህ ትጠፋለህ።

10. “ንጉሥንና አለቆችን ስጠኝ፤”ብለህ እንደ ጠየቅኸው፣ያድንህ ዘንድ ንጉሥህ የት አለ?በከተሞችህ ሁሉ የነበሩ ገዦችህስ የት አሉ?

11. በቊጣዬ ንጉሥን ሰጠሁህ፤በመዓቴም ሻርሁት።

12. የኤፍሬም በደል ተከማችቶአል፤ኀጢአቱም በመዝገብ ተይዞአል።

13. በምጥ ላይ እንዳለች ሴት ጭንቅ ይመጣበታል፤እርሱ ግን ጥበብ የሌለው ልጅ ነው፤የሚወለድበት ጊዜ ሲደርስ፣ከእናቱ ማሕፀን መውጣት የማይፈልግ ሕፃን ነው።

14. “ከመቃብር ኀይል እታደጋቸዋለሁ፤ከሞትም እቤዣቸዋለሁ፤ሞት ሆይ፤ መቅሠፍትህ የት አለ?መቃብር ሆይ፤ ማጥፋትህ የት አለ?“ከእንግዲህ ወዲህ አልራራለትም፤

15. በወንድሞቹ መካከል ቢበለጽግም እንኳ፣የምሥራቅ ነፋስ ከምድረ በዳ እየነፈሰ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ ይመጣል፤ምንጩ ይነጥፋል፤የውሃ ጒድጓዱም ይደርቃል።የከበረው ሀብቱ ሁሉ፣ከግምጃ ቤቱ ይበዘበዛል።

16. የሰማርያ ሰዎች በደላቸውን ይሸከማሉ፤በአምላካቸው ላይ ዐምፀዋልና፤በሰይፍ ይወድቃሉ፤ሕፃኖቻቸውም በምድር ላይ ይፈጠፈጣሉ፤የእርጉዝ ሴቶቻቸውም ሆድ ይቀደዳል።