ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሆሴዕ 10:11-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. ኤፍሬም ማበራየት እንደምትወድ፣እንደ ተገራች ጊደር ነው፤በተዋበ ጫንቃዋም ላይ፣ቀንበርን አኖራለሁ፤ኤፍሬምን እጠምዳለሁ፤ይሁዳ ያርሳል፤ያዕቆብም መሬቱን ያለሰልሳል።

12. ለራሳችሁ ጽድቅን ዝሩ፤የጽኑ ፍቅርን ፍሬ ዕጨዱ፤ዕዳሪውንም መሬት ዕረሱ፤እርሱም መጥቶ፣ጽድቅን በላያችሁ እስኪያዘንብ ድረስ፣ እግዚአብሔርን የምትፈልጉበት ጊዜ ነውና።

13. እናንተ ግን ክፋትን ዘራችሁ፤ኀጢአትንም ዐጨዳችሁ፤የሐሰትንም ፍሬ በላችሁ።በራሳችሁ ጒልበት፣በተዋጊዎቻችሁም ብዛት ታምናችኋልና፣

14. ሰልማን፣ ቤትአርብኤልን በጦርነት ጊዜ እንዳፈራረሰ፣እናቶችንም ከልጆቻቸው ጋር በምድር ላይ እንደ ፈጠፈጣቸው፣ሽብር በሕዝብህ ላይ ይመጣል፤ምሽጎችህም ሁሉ ይፈራርሳሉ፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሆሴዕ 10