ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 6:38-42 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

38. ተማርከው በሚኖሩበትም ምድር ሆነው በፍጹም ልባቸው፣ በፍጹምም ነፍሳቸው ቢመለሱና ለአባቶቻቸው ወደ ሰጠሃቸው ምድር፣ አንተም ወደ መረጥኻት ከተማና እኔም ለስምህ ወደ ሠራሁት ቤተ መቅደስ ቢጸልዩ፣

39. ጸሎታቸውንና ልመናቸውን በሰማይ በማደሪያህ ስማ፤ የጠየቊህንም አድርግላቸው። የበደሉህንም የሕዝብህን ኀጢአት ይቅር በል።

40. አሁንም አምላኬ ሆይ፤ በዚህ ስፍራ ወደ ቀረበው ጸሎት ዐይኖችህ የተገለጡ፣ ጆሮዎችህም የሚያደምጡ ይሁኑ።

41. “አሁንም እግዚአብሔር አምላክ ሆይ ተነሥ፣ ከኀይልህ ታቦት ጋር ወደ ማረፊያ ቦታህ ግባ። እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ ካህናትህ ድነትን ይልበሱ፤ ቅዱሳንህም በቸርነትህ ደስ ይበላቸው።

42. እግዚአብሔር አምላክ ሆይ፤ የቀባኸውን አትተወው፤ ለባሪያህ ለዳዊት ቃል የገባህለትን ጽኑ ፍቅር አስብ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ዜና መዋዕል 6