ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 3:9-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. የወርቅ ምስማሮቹም አምሳ ሰቅል ይመዝኑ ነበር፤ የላይኛውንም ክፍሎች እንደዚሁ በወርቅ ለበጠ።

10. በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የሁለት ኪሩቤል ምስል አስቀርጾ በወርቅ ለበጣቸው።

11. ከዳር እስከ ዳር ገጥሞ የተዘረጋው የኪሩቤል ክንፍ በጠቅላላው ሃያ ክንድ ነበር፤ የመጀመሪያው ኪሩብ አንዱ ክንፍ አምስት ክንድ ሆኖ የቤተ መቅደሱን ግድግዳ ሲነካ፣ ሌላው አምስት ክንድ የሆነው ክንፉ ደግሞ የሁለተኛውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።

12. እንደዚሁም የሁለተኛው ኪሩብ አንዱ ክንፍ አምስት ክንድ ሆኖ በአንጻሩ ያለውን የቤተ መቅደስ ግድግዳ ሲነካ፣ አምስት ክንድ የሆነው ሌላው ክንፉ ደግሞ የመጀመሪያውን ኪሩብ ክንፍ ይነካ ነበር።

13. የተዘረጋው የእነዚህ ኪሩቤል ክንፍ ሃያ ክንድ ሲሆን፣ ፊታቸውን ወደ ቤተ መቅደሱ ዋና ክፍል አዙረው በእግራቸው ቆመዋል።

14. ደግሞም ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከደማቅ ቀይ ፈትልና ከቀጭን በፍታ መጋረጃ ሠርቶ፣ የኪሩቤልን ምስል በጥልፍ ጠለፈበት።

15. በቤተ መቅደሱም ፊት ለፊት በአንድነት ቁመቱ ሠላሳ አምስት ክንድ የሆነ፣ በእያንዳንዱም ላይ አምስት ክንድ ጒልላት ያለው ሁለት ዐምድ ሠራ።

16. እርስ በርሳቸው የተጠላለፉ ሰንሰለቶች ሠርቶ ከዐምዶቹ ጫፍ ጋር አገናኛቸው፤ ከዚያም መቶ የሮማን ፍሬዎች ሠርቶ ከሰንሰለቶቹ ጋር አያያዛቸው።

17. ዐምዶቹንም አንዱን በደቡብ፣ ሌላውን በሰሜን አድርጎ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው፤ በደቡብ በኩል ያለውን፤ “ያኪን”፣ በሰሜን በኩል ያለውንም “ቦዔዝ” ብሎ ጠራቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ዜና መዋዕል 3