ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ዜና መዋዕል 10:13-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

13. ንጉሡም የሽማግሌዎችን ምክር በመናቅ፣ አመናጭቆ መለሰላቸው፤

14. እርሱም የወጣቶቹን ምክር በመቀበል፣ “አባቴ ቀንበራችሁን አከበደ፤ እኔ ደግሞ የባሰ አከብደዋለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገረፋችሁ፤ እኔ ደግሞ በጊንጥ እገርፋችኋለሁ” አላቸው።

15. እግዚአብሔር በሴሎናዊው በአሒያ አማካይነት ለናባጥ ልጅ ለኢዮርብዓም የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ፣ ወስኖ ስለ ነበር፣ ንጉሡ ሕዝቡን አላዳመጠም።

16. መላው እስራኤልም ንጉሡ ሊሰማቸው አለመፈለጉን በተረዱ ጊዜ፣ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፤“ከዳዊት ምን ድርሻ አለን?ከእሴይስ ልጅ ምን ክፍል አለን?እስራኤል፣ ሆይ፤ ወደ ድንኳንህ ተመለስ፤ዳዊት ሆይ፤ አንተም የገዛ ቤትህን ጠብቅ።”ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ ወደ የቤታቸው ተመለሱ።

17. ይሁን እንጂ በይሁዳ ከተሞች የሚኖሩትን እስራኤላውያን አሁንም የሚገዛቸው ሮብዓም ነበር።

18. ንጉሥ ሮብዓም የገባሮች ኀላፊ የነበረውን አዶራምን ላከው፤ እስራኤላውያን ግን በድንጋይ ወግረው ገደሉት። ንጉሥ ሮብዓም ግን እንደምንም ብሎ ሰረገላው ላይ በመውጣት ወደ ኢየሩሳሌም ሸሽቶ አመለጠ።

19. ስለዚህ እስራኤል እስከ ዛሬ ድረስ በዳዊት ቤት ላይ እንደ ዐመፀ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ዜና መዋዕል 10