ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ነገሥት 22:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ኢዮስያስ ሲነግሥ ዕድሜው ገና ስምንት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሠላሳ አንድ ዓመት ገዛ። እናቱም የባሱሮት አገር ሰው የአዳያ ልጅ ይዲዳ ነበረች።

2. ኢዮስያስም በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ፤ ወደ ቀኝም ወደ ግራም አላለም፤ አባቱ ዳዊት በሄደበት መንገድ ሁሉ ሄደ።

3. በዘመነ መንግሥቱ በዐሥራ ስምንተኛውም ዓመት ኢዮስያስ የሜሶላምን የልጅ ልጅ የኤዜልያስን ልጅ ጸሓፊውን ሳፋንን ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ላከው፤ እንዲህም አለው፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ነገሥት 22