ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ነገሥት 21:23-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. የአሞንም ሹማምት ዐመፁ፤ ንጉሡንም በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ገደሉት።

24. ከዚያም የአገሩ ሕዝብ በንጉሥ አሞን ላይ ያመፁትን ሁሉ ገደሉ፤ ልጁን ኢዮስያስንም በእግሩ ተክተው አነገሡት።

25. በአሞን ዘመነ መንግሥት የተከናወነው ሌላው ሥራ፣ የፈጸመውም ድርጊት ሁሉ በይሁዳ ነገሥታት ታሪክ ተጽፎ የሚገኝ አይደለምን?

26. እርሱም በዖዛ አትክልት ውስጥ ባለው መቃብሩ ተቀበረ፤ ልጁ ኢዮስያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ነገሥት 21