ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ነገሥት 2:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ኤልያስን በዐውሎ ነፋስ ወደ ሰማይ የሚወስድበት ጊዜ ሲደርስ፣ ኤልያስና ኤልሳዕ ከጌልገላ ተነሥተው ይጓዙ ነበር።

2. ኤልያስም ኤልሳዕን፣ “እግዚአብሔር እኔን ወደ ቤቴል ልኮኛልና አንተ በዚሁ ቈይ” አለው።ኤልሳዕ ግን፣ “ሕያው፣ እግዚአብሔርን፣ በሕያው ነፍስህም እምላለሁ ካንተ አልለይም” አለው። ስለዚህ አብረው ወደ ቤቴል ወረዱ።

3. በቤቴል የነበሩ የነቢያት ማኅበር ወደ ኤልሳዕ ወጥተው፣ “እግዚአብሔር፣ ጌታህን ኤልያስን ዛሬ ከአንተ ነጥሎ እንደሚወስደው አውቀሃልን?” አሉት።ኤልሳዕም፣ “አዎን ዐውቄአለሁ፤ እናንተ ግን ዝም በሉ” አለ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ነገሥት 2