ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ነገሥት 19:29-31 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

29. “ሕዝቅያስ ሆይ፤ ምልክቱ ይህ ነው፤“በዚህ ዓመት በገዛ እጁ የበቀለውን፣በሚመጣው ዓመት ደግሞ የገቦውን እህል ትበላላችሁ፤በሦስተኛው ዓመት ግን ትዘራላችሁ፤ ታጭዳላችሁ፤ወይንም ትተክላላችሁ፤ ፍሬውንም ትበላላችሁ።

30. አሁንም ከዳዊት ቤት የተረፉት፣ሥራቸውን ወደ ታች ይሰዳሉ፤ ወደ ላይም ፍሬ ያፈራሉ።

31. ከኢየሩሳሌም በሕይወት የተረፉት፣ከጽዮን ተራራም ከሞት ያመለጡት ይወጣሉና። የእግዚአብሔር ቅናት ይህን ታደርጋለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ነገሥት 19