ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ነገሥት 14:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእስራኤል ንጉሥ የኢዮአካዝ ልጅ ዮአስ በነገሠ በሁለተኛው ዓመት፣ የይሁዳ ንጉሥ የኢዮአስ ልጅ አሜስያስ ነገሠ።

2. በነገሠም ጊዜ ዕድሜው ሃያ አምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሃያ ዘጠኝ ዓመት ገዛ። እናቱም ዮዓዳን የተባለች የኢየሩሳሌም ሴት ነበረች።

3. እርሱም በእግዚአብሔር ፊት መልካም ነገር አደረገ፤ ነገር ግን አባቱ ዳዊት እንደ አደረገው ዐይነት አልነበረም፤ በማናቸውም ረገድ የአባቱን የኢዮአስን ፈለግ ተከተለ።

4. በየኰረብታው ላይ ያሉት ማምለኪያዎች አልተወገዱም፤ ሕዝቡም በየኰረብታው ላይ መሥዋዕት ማቅረቡንና ዕጣን ማጤሱን እንደ ቀጠለ ነበር።

5. አሜስያስ መንግሥቱን አጽንቶ ከያዘ በኋላ፣ ንጉሡን አባቱን የገደሉትን ሹማምት ገደላቸው፤

6. ይሁን እንጂ በሙሴ የሕግ መጽሐፍ እግዚአብሔር፣ “እያንዳንዱ በራሱ ኀጢአት ይገደል እንጂ አባቶች በልጆቻቸው፣ ልጆችም በአባቶቻቸው ኀጢአት አይገደሉ” ሲል ያዘዘ በመሆኑ፣ የነፍሰ ገዳዩን ልጆች አልገደላቸውም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ነገሥት 14