ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

2 ነገሥት 11:16-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ስለዚህ ፈረሶች ወደ ቤተ መንግሥቱ በሚገቡበት ስፍራ ስትደርስ፣ ይዘው እዚያው ገደሏት።

17. ዮዳሄም የእግዚአብሔር ሕዝብ ይሆኑ ዘንድ በእግዚአብሔርና በንጉሡ በሕዝቡም መካከል ቃል ኪዳን እንዲኖር አደረገ፤ እንደዚሁም በንጉሡና በሕዝቡ መካከል ቃል ኪዳን መሠረተ።

18. የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ወደ በኣል ቤተ ጣዖት ሄደው አፈራረሱት፤ መሠዊያዎቹንና ምስሎቹን ሁሉ ሰባበሩ፤ የበኣልን ካህን ማታንንም በመሠዊያዎቹ ፊት ለፊት ገደሉት።ከዚያም ካህኑ ዮዳሄ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ የሚጠብቁ ዘበኞችን መደበ።

19. ከዚያም መቶ አለቆቹን፣ ካራውያንንና ዘበኞቹን እንዲሁም የአገሩን ሕዝብ በሙሉ በመያዝ ሁሉም በአንድነት ሆነው፣ ንጉሡን ከእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወስደው በዘብ ጠባቂዎች ቅጥር በር በኩል ታች ወዳለው ቤተ መንግሥት ይዘውት ገቡ፤ ንጉሡም በዙፋኑ ላይ ተቀመጠ፤

20. የአገሩም ሕዝብ ሁሉ ደስ አለው፤ ጎቶልያ ቤተ መንግሥቱ ውስጥ በሰይፍ ተገድላ ስለ ነበር፣ ከተማዪቱ ጸጥ አለች።

21. ኢዮአስ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሰባት ዓመት ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 2 ነገሥት 11