ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 7:1-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የይሳኮር ወንዶች ልጆች፤ቶላ፣ ፉዋ፣ ያሱብ፣ ሺምሮን፤ ባጠቃላይ አራት ናቸው።

2. የቶላ ወንዶች ልጆች፤ኦዚ፣ ረፋያ፣ ይሪኤል፣ የሕማይ፣ ይብሣም፣ ሽሙኤል፤ እነዚህ የየቤተ ሰባቸው አለቆች ናቸው፤ በዳዊት ዘመነ መንግሥት ከቶላ ዘሮች፣ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩት የቶላ ዘሮች ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ ቍጥራቸውም ሃያ ሁለት ሺህ ስድስት መቶ ነበረ።

3. የኦዚ ወንድ ልጅ፤ይዝረሕያ።የይዝረሕያ ወንዶች ልጆች፤ሚካኤል፣ አብድዩ፣ ኢዩኤል፣ ይሺያ፤ አምስቱም አለቆች ነበሩ።

4. ብዙ ሚስቶችና ልጆች ስለ ነበሩአቸው፣ ከቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረግ ለውጊያ ብቁ የሆኑ ሠላሳ ስድስት ሺህ ሰዎች ነበሩአቸው።

5. ከይሳኮር ጐሣዎች ሁሉ የተመዘገቡት ተዋጊዎች የቤተ ሰቦቹ ትውልድ ቊጥር ባጠቃላይ ሰማንያ ሰባት ሺህ ነበሩ።

6. ሦስቱ የብንያም ወንዶች ልጆች፤ቤላ፣ ቤኬር፣ ይዲኤል።

7. የቤላ ወንዶች ልጆች፤ኤሴቦን፣ ኦዚ፣ ዑዝኤል፣ ኢያሪሙት፣ ዒሪ፤ ባጠቃላይ አምስት ሲሆኑ፣ የቤተ ሰብ አለቆች ናቸው፤ በትውልድ ሐረግ መዝገባቸው ሃያ ሁለት ሺህ ሠላሳ አራት ተዋጊ ሰዎች ተመዝግበዋል።

8. የቤኬር ወንዶች ልጆች፤ዝሚራ፣ ኢዮአስ፣ አልዓዛር፣ ኤልዮዔናይ፣ ዖምሪ፣ ኢያሪሙት፣ አብያ፣ ዓናቶት፣ ዓሌሜት፤ እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።

9. በትውልድ ሐረግ መዝገባቸውም ውስጥ የየቤተ ሰባቸው አለቆችና ሃያ ሺህ ሁለት መቶ ተዋጊዎች ተመዝግበዋል።

10. የይዲኤል ልጅ፤ቢልሐን።የቢልሐን ወንዶች ልጆች፤የዑስ፣ ብንያም፣ ኤሁድ፣ ክንዓና፣ ዜታን፣ ተርሴስ፣ አኪሳኦር፤

11. እነዚህ ሁሉ የይዲኤል ልጆች የየቤተ ሰቡ አለቆች ነበሩ፤ እነርሱም ለውጊያ ብቁ የሆኑ ዐሥራ ሰባት ሺህ ተዋጊዎች ነበሯቸው።

12. ሳፈንና ሑፊም የዒር ዘሮች ሲሆኑ፣ ሑሺም ደግሞ የአሔር ዘር ነው።

13. የንፍታሌም ወንዶች ልጆች፤ያሕጽሔል፣ ጉኒ፣ ዬጽር፣ ሺሌም፤ እነዚህ የባላ ዘሮች ናቸው።

14. የምናሴ ዘሮች፤ሶርያዊት ቁባቱ የወለደችለት ልጁ አሥርኤል ነው። እርሷም የገለዓድን አባት ማኪርን የወለደች ናት፤

15. ማኪርም ከሑፊምና ከሳፊም ወገኖች ሚስት አገባ። እኅቱም መዓካ ትባል ነበር።ሌላው ዘሩ ሰለጰዓድ ሲሆን፣ እርሱም ሴቶች ልጆች ብቻ ነበሩት።

16. የሚኪር ሚስት መዓካ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ፋሬስ አለችው። የወንድሙም ስም ሱሮስ ይባላል፤ ወንዶች ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 7