ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 4:21-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

21. የይሁዳ ልጅ የሴሎም ወንዶች ልጆች፤የሌካ አባት ዔር፣ የመሪሳና በቤት አሽቤዓ የበፍታ ጨርቅ ሠሪ የሆኑት ጐሣዎች አባት ለዓዳ፣

22. ዮቂም፣ የኮዜባ ሰዎች፣ ኢዮአስ፣ ሞዓብን የገዛ ሣራፍና ያሹቢሌሔም። ታሪካቸውም ጥንታዊነት ያለው ነው።

23. ሰዎቹ በነጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠሪዎች ነበሩ፤ በዚያም በመቀመጥ ለንጉሡ ሸክላ ይሠሩ ነበር።

24. የስምዖን ዘሮች፤ነሙኤል፣ ያሚን፣ ያሪን፣ ዛራ፣ ሳኡል፤

25. ሰሎም የሳኡል ልጅ ነው፤ መብሳም የሰሎም ልጅ ነው፤ማስማዕ ደግሞ የመብሳም ልጅ ነው።

26. የማስማዕ ዘሮችልጁ ሃሙኤል፣ ልጁ ዘኩር፣ ልጁ ሰሜኢ።

27. ሰሜኢ ዐሥራ ስድስት ወንዶችና ስድስት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ ወንድሞቹ ግን ብዙ ልጆች አልነበሯቸውም፤ ስለዚህ ጐሣቸው በሙሉ እንደ ይሁዳ ሕዝብ ብዙ አልነበረም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 4