ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 4:2-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. የሦባል ልጅ ራያ ኢኤትን ወለደ፤ ኢኤት ደግሞ አሑማይንና ላሃድን ወለደ፤ እነዚህም የጾርዓውያን ጐሣዎች ናቸው።

3. የኤጣም ወንዶች ልጆች እነዚህ ናቸው፤ ኢይዝራኤል፣ ይሽማ፣ ይደባሽ። እኅታቸው ሃጽሌልፎኒ ትባላለች።

4. ፋኑኤል ጌዶርን ወለደ፤ ኤጽር ደግሞ ሑሻምን ወለደ። እነዚህ የኤፍራታ የበኵር ልጅና የቤተ ልሔም አባት የሆነው የሆር ዘሮች ናቸው።

5. የቴቁሔ አባት አሽሑር፣ ሔላና ነዕራ የተባሉ ሁለት ሚስቶች ነበሩት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 4