ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 4:19-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

19. የሆዲያ ሚስት የነሐም እኅት ወንዶች ልጆች፤የገርሚው የቅዒላ አባት፣ ማዕካታዊው ኤሽትሞዓ።

20. የሺሞን ወንዶች ልጆች፤አምኖን፣ ሪና፣ ቤንሐናን፣ ቲሎን። የይሺዒ ዘሮች፤ ዞሔትና ቤንዞሔት።

21. የይሁዳ ልጅ የሴሎም ወንዶች ልጆች፤የሌካ አባት ዔር፣ የመሪሳና በቤት አሽቤዓ የበፍታ ጨርቅ ሠሪ የሆኑት ጐሣዎች አባት ለዓዳ፣

22. ዮቂም፣ የኮዜባ ሰዎች፣ ኢዮአስ፣ ሞዓብን የገዛ ሣራፍና ያሹቢሌሔም። ታሪካቸውም ጥንታዊነት ያለው ነው።

23. ሰዎቹ በነጣዒምና በጋዴራ የሚቀመጡ ሸክላ ሠሪዎች ነበሩ፤ በዚያም በመቀመጥ ለንጉሡ ሸክላ ይሠሩ ነበር።

24. የስምዖን ዘሮች፤ነሙኤል፣ ያሚን፣ ያሪን፣ ዛራ፣ ሳኡል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 4