ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 21:5-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

5. ኢዮአብም የተዋጊዎቹን ሰዎች ቍጥር ለዳዊት አቀረበ፤ እነዚህም በመላው እስራኤል አንድ ሚሊዮን አንድ መቶ ሺህ፣ በይሁዳ ደግሞ አራት መቶ ሰባ ሺህ ሲሆኑ፣ ሁሉም ሰይፍ መምዘዝ የሚችሉ ነበሩ።

6. ኢዮአብ ግን የንጉሡ ትእዛዝ አስጸያፊ ነበረና፣ የሌዊንና የብንያምን ነገድ ጨምሮ አልቈጠረም።

7. ይህ ትእዛዝ በእግዚአብሔር ዘንድ የተጠላ ነበር፤ ስለዚህ እግዚአብሔር እስራኤልን ቀጣ።

8. ከዚያም ዳዊት እግዚአብሔርን፣ “ይህን በማድረጌ እጅግ በድያለሁ፤ የፈጸምሁትም የስንፍና ሥራ ስለ ሆነ፣ የባሪያህን በደል እንድታስወግድ እለምንሃለሁ” አለ።

9. እግዚአብሔርም የዳዊት ባለ ራእይ የሆነውን ጋድን እንዲህ አለው፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 21