ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 2:23-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ይሁን እንጂ ጌሹርና አራም፣ ቄናትንና በዙሪያዋ የሚገኙትን ሥልሳ መንደሮች ጨምሮ የኢያዕርን ከተሞች ነጠቁት። እነዚህ ሁሉ የገለዓድ አባት የማኪር ዘሮች ነበሩ።

24. ኤስሮም በካሌብ ኤፍራታ ከሞተ በኋላ፣ ሚስቱ አቢያ የቴቁሔን አባት አሽሑርን ወለደችለት።

25. የኤስሮም የበኵር ልጅ የይረሕምኤል ወንዶች ልጆች፤የበኵር ልጁ ራም፣ ቡናህ፣ ኦሬን፣ ኦጼም፣ አኪያ።

26. ይረሕምኤል ዓጣራ የተባለች ሌላ ሚስት ነበረችው፤ እርሷም የኦናምን እናት ነበረች።

27. የይረሕምኤል የበኵር ልጁ የራም ወንዶች፤መዓስ፣ ያሚን፣ ዔቄር።

28. የኦናም ወንዶች ልጆች፤ሸማይና ያዳ።የሸማይ ወንዶች ልጆች፤ናዳብና አቢሱር።

29. የአቢሱር ሚስት አቢካኢል ትባላለች፤ እርሷም አሕባንንና ሞሊድ የተባሉ ልጆች ወለደችለት።

30. የናባድ ወንዶች ልጆች፤ሴሌድ፣ አፋይም፤ ሴሌድ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ሞተ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 2