ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 16:9-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ዘምሩለት፤ ውዳሴም አቅርቡለት፤ድንቅ ሥራውን ሁሉ ንገሩ፤

10. በቅዱስ ስሙ ተጓደዱ፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉ ሁሉ፣ ልባቸው ሐሤት ያድርግ።

11. ወደ እግዚአብሔርና ወደ ኀይሉ ተመልከቱ፤ዘወትር ፊቱን ፈልጉ።

12. ያደረጋቸውን ድንቅ ሥራዎች፣ታምራቱንና የሰጠውንም ፍርድ አስታውሱ፤

13. እናንተ የባሪያው የእስራኤል ዘሮች፣እናንተ የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች።

14. እርሱ እግዚአብሔር አምላካችን ነው፤ፍርዱም በምድር ሁሉ ላይ ነው፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 16