ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 16:17-22 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

17. ይህንንም ለያዕቆብ ሥርዐት አድርጎ አጸና፤ለእስራኤልም የዘላለም ኪዳን አደረገ፤

18. እንዲህ ሲል፣ “የምትወርሰው ርስት እንዲሆን፣የከነዓንን ምድር ለአንተ እሰጣለሁ።”

19. ቍጥራቸው ገና ጥቂት ሳለ፣በእርግጥ ጥቂትና መጻተኞች ሳሉ፣

20. ከአንዱ ሕዝብ ወደ ሌላው ሕዝብ፣ከአንዱም መንግሥት ወደ ሌላው መንግሥት ተንከራተቱ።

21. ማንም እንዲጨቍናቸው አልፈቀደም፤ስለ እነርሱም ነገሥታትን ገሠጸ፤

22. እንዲህ ሲል፤ “የቀባኋቸውን አትንኩ፤በነቢያቴ ላይ ክፉ አታድርጉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 16