ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 15:3-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ዳዊት የእግዚአብሔርን ታቦት ወዳዘጋጀለት ስፍራ እንዲያመጡ እስራኤልን ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰበሰበ።

4. የአሮንን ዘሮችና ሌዋውያኑንም በአንድነት ሰበሰበ፤

5. ከቀዓት ዘሮች፣አለቃውን ኡርኤልንና አንድ መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤

6. ከሜራሪ ዘሮች፣አለቃውን ዓሣያንና ሁለት መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤

7. ከጌድሶን ዘሮች፣አለቃውን ኢዮኤልንና አንድ መቶ ሠላሳ የሥጋ ዘመዶቹን፤

8. ከኤሊጻፋን ዘሮች፣አለቃውን ሸማያንና ሁለት መቶ የሥጋ ዘመዶቹን፤

9. ከኬብሮን ዘሮች፣አለቃውን ኤሊኤልንና ሰማንያ የሥጋ ዘመዶቹን፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 15