ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ዜና መዋዕል 15:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ዳዊት በስሙ በተጠራችው ከተማ ለራሱ ቤቶችን ሠራ፤ ለእግዚአብሔር ታቦት ቦታ አዘጋጅቶ ድንኳን ተከለ።

2. ከዚያም ዳዊት፣ “የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙና ለዘላለም በፊቱ እንዲያገለግሉ እግዚአብሔር ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር፣ የእግዚአብሔርን ታቦት ማንም አይሸከም” ሲል አዘዘ።

3. ዳዊት የእግዚአብሔርን ታቦት ወዳዘጋጀለት ስፍራ እንዲያመጡ እስራኤልን ሁሉ በኢየሩሳሌም ሰበሰበ።

4. የአሮንን ዘሮችና ሌዋውያኑንም በአንድነት ሰበሰበ፤

5. ከቀዓት ዘሮች፣አለቃውን ኡርኤልንና አንድ መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤

6. ከሜራሪ ዘሮች፣አለቃውን ዓሣያንና ሁለት መቶ ሃያ የሥጋ ዘመዶቹን፤

7. ከጌድሶን ዘሮች፣አለቃውን ኢዮኤልንና አንድ መቶ ሠላሳ የሥጋ ዘመዶቹን፤

8. ከኤሊጻፋን ዘሮች፣አለቃውን ሸማያንና ሁለት መቶ የሥጋ ዘመዶቹን፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ዜና መዋዕል 15