ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ነገሥት 7:43-49 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

43. ዐሥሩን የዕቃ ማስቀመጫዎች፣ ከዐሥር መታጠቢያ ገንዳዎቻቸው ጋር፤

44. ገንዳውንና በሥሩ ያሉትን ዐሥራ ሁለት በሬዎች፤

45. ድስቶችን፣ መጫሪያዎችንና ጐድጓዳ ሳሕኖችን።ኪራም ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት እንዲውሉ እነዚህን ዕቃዎች ሁሉ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራለት ከተወለወለና ከሚብረቀረቅ ናስ ነበር።

46. ንጉሡም እነዚህን በማቅለጥ በሸክላ ቅርጽ ውስጥ ፈሰው እንዲወጡ ያደረገው በሱኮትና በጻርታን መካከል ባለው በዮርዳኖስ ሸለቆ ነበር።

47. ሰሎሞን ከብዛታቸው የተነሣ እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች እንዲመዘኑ አላደረገም፣ ስለዚህም የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደ ነበረ አልታወቀም።

48. እንዲሁም ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አግልግሎት እንዲውሉ ከዚህ የሚከተሉትን ዕቃዎች ሁሉ ሠራ፤የወርቅ መሠዊያን፣ገጸ ኅብስቱ የሚቀመጥበትን የወርቅ ጠረጴዛ፤

49. በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት አምስቱ በቀኝ፣ አምስቱ በግራ የሚቀመጡ፣ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መቅረዞችን፣ ከወርቅ የተሠሩአበቦችን፣ የመብራት ቀንዲሎችንና መቈስቈሻዎችን፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ነገሥት 7