ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ነገሥት 4:14-24 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

14. የዒዶ ልጅ አሒናዳብ፤ በማሃናይም፣

15. አኪማአስ በንፍታሌም፣ እርሱምየሰሎሞንን ልጅ ባስማትን አግብቶየነበረ ነው፤

16. የኩሲ ልጅ በዓና፤ በአሴርና በበዓሎት፣

17. የፋሩዋ ልጅ ኢዮሣፍጥ በይሳኮር፣

18. የኤላ ልጅ ሳሚ በብንያም፣

19. የኡሪ ልጅ ጌበር፤በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፣በባሳን ንጉሥ በዐግ አገር፣ እርሱምየአውራጃው ብቸኛ ገዥ ነበር።

20. የይሁዳና የእስራኤል ሕዝቦች ብዛታቸው እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ሆነ፤ ይበሉ፣ ይጠጡና ይደሰቱም ነበር።

21. ሰሎሞንም ከወንዙ አንሥቶ እስከ ፍልስጥኤማውያን ምድር፣ ከዚያም እስከ ግብፅ ዳርቻ ያሉትን መንግሥታት ሁሉ ገዛ፤ እነዚህም አገሮች ግብር አመጡለት፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ተገዙለት።

22. ለሰሎሞን በየቀኑ የሚገባለትም ቀለብ ይህ ነበር፤ ሠላሳ ኮር ማለፊያ ዱቄት፣ ሥልሳ ኮር መናኛ ዱቄት፣

23. ዐሥር ቅልብ ሰንጋዎች፣ ሃያ ግጦሽ መሬት ላይ የሚውሉ በሬዎች፣ መቶ በግና ፍየል እንዲሁም ዋሊያ፣ ሚዳቋ፣ የበረሓ ፍየልና ምርጥ አዕዋፍ።

24. ከወንዙ በስተ ምዕራብ፣ ከቲፍሳ እስከ ጋዛ ያሉትን መንግሥታት ስለ ገዛ፣ በሁሉም አቅጣጫ ሰላም ሆኖለት ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ነገሥት 4