ምዕራፎች

  1. 1
  2. 2
  3. 3
  4. 4
  5. 5
  6. 6
  7. 7
  8. 8
  9. 9
  10. 10
  11. 11
  12. 12
  13. 13
  14. 14
  15. 15
  16. 16
  17. 17
  18. 18
  19. 19
  20. 20
  21. 21
  22. 22

ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ነገሥት 4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

የሰሎሞን ሹማምት

1. ንጉሥ ሰሎሞን በእስራኤል ሁሉ ላይ ነገሠ፤

2. ዋና ዋናዎቹ ሹማምቱም እነዚህ ነበሩ፤የሳዶቅ ልጅ ዓዛርያስ፣ ካህን፤

3. የሺሻ ልጆች ኤሊሖሬፍናአኪያ፣ ጸሓፊዎች፤የአሒሉድ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣ ታሪክ ጸሓፊ፤

4. የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ የሰራዊቱ ዋና አዛዥ፤ሳዶቅና አብያታር፣ ካህናት፤

5. የናታን ልጅ ዓዛርያስ፣ የአውራጃገዦች የበላይ ኀላፊ፤የናታን ልጅ ዛቡድ፣ ካህንና የንጉሡየቅርብ አማካሪ፤

6. አሒሳር፣ የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፤የዓብዳ ልጅ አዶኒራም የግዳጅ ሥራተቈጣጣሪ።

7. እንዲሁም ሰሎሞን ለንጉሡና ለንጉሡ ቤት የሚሆነውን ቀለብ ከመላው እስራኤል የሚሰበስቡ ዐሥራ ሁለት የአውራጃ ገዦች ነበሩት፤ እነዚህም እያንዳንዳቸው በዓመት ውስጥ የወር ቀለብ የሚያቀርቡ ነበሩ።

8. ስማቸውም እንደሚከተለው ነው፤ቤንሑር፣ በኰረብታማው በኤፍሬምምድር፤

9. ቤንጼቄር፣ በማቃጽ፣ በሻዓልቢም፣በቤትሳሜስ፣ በኤሎንቤትሐናን፤

10. ቤንሔሴድ፣ በአሩቦት ውስጥየሚገኙት ሰኰትና የኦፌር አገርበሙሉ የእርሱ ነበር፤

11. ቤን አሚናዳብ፤ በናፎትረ ዶር፣እርሱም የሰሎሞንን ልጅ ጣፈትንአግብቶ የነበረ ነው፤

12. የአሒሉድ ልጅ በዓና፣ በታዕናክናበመጊዶ እንዲሁም ከጻርታን ቀጥሎቍልቍል እስከ ኢይዝራኤል ባለውበቤትሳን ሁሉ፣ ከዚያም ዮቅምዓምንተሻግሮ እስከ አቤልምሖላና ድረስ፣

13. ቤንጌበር፣ በገለዓድ ራሞት ከተማእዚያው ገለዓድ ውስጥ የምናሴልጅ የኢያዕር መንደሮች፣ በባሳንምየአርጎብ አውራጃ እንዲሁም በሮቻቸው የናስ መወርወሪያ በሆኑ ሥልሳባለ ቅጥር ታላላቅ ከተሞች፤

14. የዒዶ ልጅ አሒናዳብ፤ በማሃናይም፣

15. አኪማአስ በንፍታሌም፣ እርሱምየሰሎሞንን ልጅ ባስማትን አግብቶየነበረ ነው፤

16. የኩሲ ልጅ በዓና፤ በአሴርና በበዓሎት፣

17. የፋሩዋ ልጅ ኢዮሣፍጥ በይሳኮር፣

18. የኤላ ልጅ ሳሚ በብንያም፣

19. የኡሪ ልጅ ጌበር፤በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፣በባሳን ንጉሥ በዐግ አገር፣ እርሱምየአውራጃው ብቸኛ ገዥ ነበር።

ለሰሎሞን በየቀኑ የሚገባለት ቀለብ

20. የይሁዳና የእስራኤል ሕዝቦች ብዛታቸው እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ሆነ፤ ይበሉ፣ ይጠጡና ይደሰቱም ነበር።

21. ሰሎሞንም ከወንዙ አንሥቶ እስከ ፍልስጥኤማውያን ምድር፣ ከዚያም እስከ ግብፅ ዳርቻ ያሉትን መንግሥታት ሁሉ ገዛ፤ እነዚህም አገሮች ግብር አመጡለት፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ተገዙለት።

22. ለሰሎሞን በየቀኑ የሚገባለትም ቀለብ ይህ ነበር፤ ሠላሳ ኮር ማለፊያ ዱቄት፣ ሥልሳ ኮር መናኛ ዱቄት፣

23. ዐሥር ቅልብ ሰንጋዎች፣ ሃያ ግጦሽ መሬት ላይ የሚውሉ በሬዎች፣ መቶ በግና ፍየል እንዲሁም ዋሊያ፣ ሚዳቋ፣ የበረሓ ፍየልና ምርጥ አዕዋፍ።

24. ከወንዙ በስተ ምዕራብ፣ ከቲፍሳ እስከ ጋዛ ያሉትን መንግሥታት ስለ ገዛ፣ በሁሉም አቅጣጫ ሰላም ሆኖለት ነበር።

25. በሰሎሞን ዘመን ሁሉ ከዳን አንሥቶ እስከ ቤርሳቤህ ያለው ይሁዳና እስራኤል፣ እያንዳንዱ ሰው ከወይኑና ከበለሱ ጥላ ሥር በሰላም ለመኖር በቃ።

26. ሰሎሞን ሠረገላ የሚጐትቱ ፈረሶች የሚያድሩበት አራት ሺህ ጋጣና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች ነበሩት።

27. የየአውራጃው ሹማምትም በየወር ተራቸው ንጉሡን ሰሎሞንንና ወደ ንጉሡ ማእድ የሚቀርቡትን ሁሉ ምንም ሳያጓድሉ ይቀልቡ ነበር፤

28. እንዲሁም ለሠረገላ ፈረሶችና ለፈጣን ፈረሶች የተመደበውን ገብስና ጭድ ከተፈለገው ቦታ ድረስ ያመጡ ነበር።

የሰሎሞን ጥበብ

29. አምላክ ለሰሎሞን ጥበብንና እጅግ ታላቅ ማስተዋልን እንዲሁም በባሕር ዳር እንዳለ አሸዋ የልብ ስፋትን ሰጠው።

30. የሰሎሞን ጥበብ ከምሥራቅ ሰዎች ሁሉ ጥበብ በጣም የላቀ ከግብፅም ጥበብ ሁሉ የበለጠ ነበር፤

31. እርሱም ከማንም ሰው ይልቅ ጥበበኛ ነበር፣ ከኢይዝራኤላዊው ከኤታን፣ ከማሖል ልጆች ከሄማንና ከከልቀድ ደግሞም ከደራል ይልቅ ጥበበኛ ነበር፤ ዝናውም በዙሪያው ባሉት አሕዛብ ሁሉ ተሰማ።

32. እርሱም ሦስት ሺህ ምሳሌዎችን ተናገረ፤ የመሓልዩም ቍጥር ሺህ አምስት ነበር።

33. ከሊባኖስ ዝግባ አንሥቶ በቅጥር ግንብ ላይ እስከሚበቅለው ሂሶጵ ስለ ዕፀዋት ተናግሮአል፤ እንዲሁም ስለ እንስሳት፣ ስለ ወፎች፣ በሆዳቸው ስለሚሳቡ እንስሳትና ስለ ዓሦችም ተናግሮአል፤

34. ጥበቡን ከሰሙት ከዓለም ነገሥታት ሁሉ የተላኩ፣ የየአገሩ ሰዎች ሁሉ የሰሎሞንን ጥበብ ለማድመጥ መጡ።