ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ነገሥት 4:12-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. የአሒሉድ ልጅ በዓና፣ በታዕናክናበመጊዶ እንዲሁም ከጻርታን ቀጥሎቍልቍል እስከ ኢይዝራኤል ባለውበቤትሳን ሁሉ፣ ከዚያም ዮቅምዓምንተሻግሮ እስከ አቤልምሖላና ድረስ፣

13. ቤንጌበር፣ በገለዓድ ራሞት ከተማእዚያው ገለዓድ ውስጥ የምናሴልጅ የኢያዕር መንደሮች፣ በባሳንምየአርጎብ አውራጃ እንዲሁም በሮቻቸው የናስ መወርወሪያ በሆኑ ሥልሳባለ ቅጥር ታላላቅ ከተሞች፤

14. የዒዶ ልጅ አሒናዳብ፤ በማሃናይም፣

15. አኪማአስ በንፍታሌም፣ እርሱምየሰሎሞንን ልጅ ባስማትን አግብቶየነበረ ነው፤

16. የኩሲ ልጅ በዓና፤ በአሴርና በበዓሎት፣

17. የፋሩዋ ልጅ ኢዮሣፍጥ በይሳኮር፣

18. የኤላ ልጅ ሳሚ በብንያም፣

19. የኡሪ ልጅ ጌበር፤በአሞራውያን ንጉሥ በሴዎን ምድር፣በባሳን ንጉሥ በዐግ አገር፣ እርሱምየአውራጃው ብቸኛ ገዥ ነበር።

20. የይሁዳና የእስራኤል ሕዝቦች ብዛታቸው እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ሆነ፤ ይበሉ፣ ይጠጡና ይደሰቱም ነበር።

21. ሰሎሞንም ከወንዙ አንሥቶ እስከ ፍልስጥኤማውያን ምድር፣ ከዚያም እስከ ግብፅ ዳርቻ ያሉትን መንግሥታት ሁሉ ገዛ፤ እነዚህም አገሮች ግብር አመጡለት፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ተገዙለት።

22. ለሰሎሞን በየቀኑ የሚገባለትም ቀለብ ይህ ነበር፤ ሠላሳ ኮር ማለፊያ ዱቄት፣ ሥልሳ ኮር መናኛ ዱቄት፣

23. ዐሥር ቅልብ ሰንጋዎች፣ ሃያ ግጦሽ መሬት ላይ የሚውሉ በሬዎች፣ መቶ በግና ፍየል እንዲሁም ዋሊያ፣ ሚዳቋ፣ የበረሓ ፍየልና ምርጥ አዕዋፍ።

24. ከወንዙ በስተ ምዕራብ፣ ከቲፍሳ እስከ ጋዛ ያሉትን መንግሥታት ስለ ገዛ፣ በሁሉም አቅጣጫ ሰላም ሆኖለት ነበር።

25. በሰሎሞን ዘመን ሁሉ ከዳን አንሥቶ እስከ ቤርሳቤህ ያለው ይሁዳና እስራኤል፣ እያንዳንዱ ሰው ከወይኑና ከበለሱ ጥላ ሥር በሰላም ለመኖር በቃ።

26. ሰሎሞን ሠረገላ የሚጐትቱ ፈረሶች የሚያድሩበት አራት ሺህ ጋጣና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች ነበሩት።

27. የየአውራጃው ሹማምትም በየወር ተራቸው ንጉሡን ሰሎሞንንና ወደ ንጉሡ ማእድ የሚቀርቡትን ሁሉ ምንም ሳያጓድሉ ይቀልቡ ነበር፤

28. እንዲሁም ለሠረገላ ፈረሶችና ለፈጣን ፈረሶች የተመደበውን ገብስና ጭድ ከተፈለገው ቦታ ድረስ ያመጡ ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ነገሥት 4