ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ነገሥት 3:26-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. በሕይወት ያለው ልጅ እናት ለልጇ እጅግ ስለ ራራች ንጉሡን፣ “ጌታዬ ሆይ፤ እባክህ በሕይወት ያለውን ሕፃን ለእርሷ ስጣት፤ አትግደለው” አለች።ሌላዪቱ ግን፣ “ለእኔም ሆነ ለአንቺ አይሰጥም፤ ሁለት ላይ ይከፈል!” አለች።

27. ከዚህ በኋላ ንጉሡ፣ “በሉ በሕይወት ያለውን ሕፃን ለመጀመሪያዪቱ ሴት ስጧት፤ አትግደሉት፤ እናቱ እርሷ ናት” አለ።

28. እስራኤላውያን ሁሉ ንጉሡ የሰጠውን ፍርድ ሲሰሙ ፈሩት፤ ፍትሕ ለመስጠት የአምላክን ጥበብ የታደለ መሆኑን አይተዋልና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ነገሥት 3