ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ሳሙኤል 30:25-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

25. ዳዊትም ከዚያ ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ይህን ለእስራኤል ደንብና ሥርዐት አደረገው።

26. ዳዊት ወደ ጺቅላግ በመጣ ጊዜ፣ ወዳጆቹ ለሆኑት ለይሁዳ ሽማግሌዎች፣ “ከእግዚአብሔር ጠላቶች የተገኘ ስጦታ እነሆ፤” በማለት ከምርኮው ላይ ከፍሎ ላከላቸው።

27. ይህንም፣ በቤቴል፣ በደቡብ ራሞትና በየቲር ለነበሩ፣

28. በኦሮዔር፣ በሢፍሞት፣ በኤሽትሞዓና

29. በራካል እንዲሁም በይረሕምኤላውያንና በቄናውያን ከተሞች ለሚኖሩ፣

30. በሔርማ፣ በቦራሣን፣ በዓታክ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ሳሙኤል 30