ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ሳሙኤል 21:3-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. ታዲያ አሁን በእጅህ ምን አለ? አምስት እንጀራ ወይም የተገኘውን ማንኛውንም ነገር ስጠኝ።”

4. ካህኑም፣ “ሰው ሁሉ የሚበላው እንጀራ የለኝም፤ ነገር ግን ሰዎቹ በቅርቡ ከሴት የተጠበቁ ከሆነ፣ የተቀደሰ እንጀራ በዚህ አለ” አለው።

5. ዳዊትም “እንደተለመደው ሁሉ ከወጣሁ ጊዜ ጀምሮ ሴቶች ከእኛ ተጠብቀዋል፤ ባል ተቀደሰ ተልእኮ ውስጥ እንኳ የሰዎቹ ዕቃዎች የተቀደሱ ናቸው፤ ታዲያ ዛሬማ እንዴት!” ሲል መለሰ።

6. ስለዚህ ካህኑ የተቀደሰውን እንጀራ ለዳዊት ሰጠው፤ ከእግዚአብሔር ፊት ተነሥቶ በትኩስ እንጀራ ከተተካው ከኅብስተ ገጹ በስተቀር በዚያ ሌላ እንጀራ አልነበረምና።

7. በዚያችም ዕለት ከሳኦል አገልጋዮች አንዱና የእረኞቹ አለቃ የሆነው ኤዶማዊው ዶይቅ እዚያው በእግዚአብሔር ፊት እንዲቈይ ተገዶ ነበር።

8. ዳዊት አቢሜሌክን፣ “የንጉሡ ጒዳይ ስላ ስቸኮለኝ፣ ሰይፌንም ሆነ ሌላ የጦር መሣሪያ አላመጣሁም፤ እዚህ ካንተ ዘንድ ጦር ወይም ሰይፍ አይገኝምን?” ሲል ጠየቀው።

9. ካህኑም፣ “በኤላ ሸለቆ አንተ የገደልኸው የፍልስጥኤማዊው የጎልያድ ሰይፍ እዚህ አለ፤ ከኤፉዱ በስተ ኋላ በጨርቅ ተጠቅልሎአል ከፈለግህ ውሰደው፤ ከእርሱ በስተቀር ሌላ ሰይፍ እዚህ የለም” ብሎ መለሰለት።ዳዊትም “እንደ እርሱ ያለ የለምና እርሱኑ ስጠኝ” አለው።

10. በዚያች ዕለት ዳዊት ከሳኦል ሸሽቶ ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አንኩስ ሄደ።

11. የአንኩስ አገልጋዮችም፣ “የምድሪቱ ንጉሥ ዳዊት ይህ አይደለምን? ደግሞስ“ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ፤ ዳዊት ግን ዐሥር ሺህ ገደለ’ብለው በጭፈራቸው የዘፈኑለትስ እርሱ አይደለምን?” አሉት።

12. ዳዊት ነገሩን በልቡ አኖረ፤ የጌትን ንጉሥ አንኩስንም እጅግ ፈራው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ሳሙኤል 21