ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ሳሙኤል 21:10-15 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. በዚያች ዕለት ዳዊት ከሳኦል ሸሽቶ ወደ ጌት ንጉሥ ወደ አንኩስ ሄደ።

11. የአንኩስ አገልጋዮችም፣ “የምድሪቱ ንጉሥ ዳዊት ይህ አይደለምን? ደግሞስ“ ‘ሳኦል ሺህ ገደለ፤ ዳዊት ግን ዐሥር ሺህ ገደለ’ብለው በጭፈራቸው የዘፈኑለትስ እርሱ አይደለምን?” አሉት።

12. ዳዊት ነገሩን በልቡ አኖረ፤ የጌትን ንጉሥ አንኩስንም እጅግ ፈራው።

13. ስለዚህ በፊታቸው አእምሮውን እንደሳተ ሰው ሆነ፤ በያዙትም ጊዜ የከተማዪቱን ቅጥሮች እየቦጫጨረ፣ ልጋጉንም በጢሙ ላይ እያዝረበረበ እንደ እብድ ሆነ።

14. አንኩስም አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፤ “ሰውየውን እስቲ ተመልከቱት፤ እብድ እኮ ነው! ታዲያ ወደ እኔ ያመጣችሁት ለምንድን ነው?

15. በፊቴ እንዲህ ይሆን ዘንድ ይህን ሰው እዚህ ያመጣችሁት እብድ አጥቼ ነውን? እንዲህ ያለውስ ሰው ወደ ቤቴ መግባት ይገባዋልን?”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ሳሙኤል 21