ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ሳሙኤል 2:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ሐናም እንዲህ ብላ ጸለየች፤“ልቤ በእግዚአብሔር ጸና፤ቀንዴም በእግዚአብሔር ከፍ ከፍ አለ፤አፌ በጠላቶቼ ላይ ተከፈተ፤በማዳንህ ደስ ይለኛልና።

2. “እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ማንም የለም፤ከአንተም በቀር ሌላ የለም፤እንደ አምላካችን ያለ ዐለት የለም።

3. “ይህን ያህል በመታበይ አትናገሩ፤እንዲህ ያለውም የእብሪት ቃል ከአፋችሁ አይውጣ፤ እግዚአብሔር አምላክ ዐዋቂ ነውና፤ሥራም ሁሉ በእርሱ ይመዘናል።

4. “የኀያላን ቀስቶች ተሰባብረዋል፤ደካሞች ግን በኀይል ታጥቀዋል።

5. ጠግበው የነበሩ ለእንጀራ ሲሉ ተገዙ፤ተርበው የነበሩ ግን እንጀራ ጠገቡ፤መካኒቱ ሰባት ልጆች ወልዳለች፤ብዙ ወንዶች ልጆች ወልዳ የነበረችው ግን መከነች።

6. “እግዚአብሔር ይገድላል፤ ያድናልም፤ወደ መቃብር ያወርዳል፤ ያወጣልም።

7. እግዚአብሔር ያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤ያዋርዳል፤ ከፍ ከፍም ያደርጋል።

8. እርሱ ድኻውን ከትቢያ ያነሣል፤ምስኪኑንም ከጒድፍ ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ከመኳንንቱ ጋር ያስቀምጣቸዋል፤የክብር ዙፋንም ያወርሳቸዋል።“የምድር መሠረቶች የእግዚአብሔር ናቸውና፣ዓለምን በእነርሱ ላይ አድርጎአል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ሳሙኤል 2