ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

1 ሳሙኤል 18:11-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እርሱም፣ “ዳዊትን ከግድግዳው ጋር አጣብቀዋለሁ” ብሎ በማሰብ ጦሩን ወረወረበት፤ ዳዊት ግን ሁለት ጊዜ ከፊቱ ዘወር አለ።

12. እግዚአብሔር ከእርሱ ተለይቶ ከዳዊት ጋር ስለ ሆነ፣ ሳኦል ዳዊትን ፈራው።

13. ስለዚህ ዳዊትን ከአጠገቡ በማራቅ የሺህ አለቃ አደረገው። ዳዊትም ሰራዊቱን እየመራ በፊታቸው ይወጣና ይገባ ነበር።

14. እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ነበር የሚያደርገው ነገር ሁሉ ይሳካለት ነበር።

15. ሳኦልም፣ ዳዊት እንደ ተሳካለት ባየ ጊዜ ፈራው፤

16. መላው እስራኤልና ይሁዳ ግን ዳዊትን ወደዱት፤ በፊታቸው እየወጣና እየገባ የሚመራቸው እርሱ ነበርና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ 1 ሳሙኤል 18