መጥተውም በጽዮን ተራራ ላይ በደስታ ይዘምራሉ፤ በእግዚአብሔርም ልግስና፣በእህሉ፣ በወይን ጭማቂውና በዘይቱ፣በፍየልና በበግ ጠቦት፣ በወይፈንና በጊደር ደስ ይሰኛሉ፤ውሃ እንደማይቋረጥባት የአትክልት ስፍራ ይሆናሉ፤ከእንግዲህም አያዝኑም።