እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“ስለ ሦስቱ የኤዶም ኀጢአት፣ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቊጣዬን አልመልስም፤ርኅራኄን በመንፈግ፣ወንድሙን በሰይፍ አሳዶታልና፤የቊጣውንም ነበልባል ሳይገድብ፣መዓቱን ሳያቋርጥ አውርዶበታልና፤