ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ዮሐንስ 7:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፣ በዚያ የነበሩት አይሁድ ሊገድሉት ስለ ፈለጉ፣ በይሁዳ አውራጃ መዘዋወር ትቶ በገሊላ ተዘዋወረ።

2. የአይሁድ የዳስ በዓል በተቃረበ ጊዜ ግን፣

3. የኢየሱስ ወንድሞች እንዲህ አሉት፤ “ደቀ መዛሙርትህም ደግሞ የምታደርገውን ታምራት እንዲያዩ፣ ከዚህ ወደ ይሁዳ ሂድ፤

4. ራሱን ሊገልጥ እየፈለገ በስውር የሚሠራ ማንም የለምና። አንተም እነዚህን ነገሮች የምታደርግ ከሆነ፣ ራስህን ለዓለም ግለጥ።”

5. የገዛ ወንድሞቹ እንኳ አላመኑበትም ነበር።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ዮሐንስ 7